Bible Verses by Topic

ተአምራት በአዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 20:29-34
ከኢያሪኮም ሲወጡ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። እነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን ብለው ጮኹ። ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን። ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን እያሉ አብዝተው ጮኹ። ኢየሱስም ቆሞ ጠራቸውና። ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ? አለ። ጌታ ሆይ፥ ዓይኖቻችን ይከፈቱ ዘንድ አሉት። ኢየሱስም አዘነላቸውና ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ፥ ወዲያውም አዩና ተከተሉት።
30
Pause     Prev     Next