Bible Verses by Topic

እግዚአብሔርን ስለ መፈለግ

2ኛ ዜና 30:18-20
እንደ ትእዛዙም ሳይሆን ከኤፍሬምና ከምናሴ ከይሳኮርና ከዛብሎንም ወገን እጅግ ሰዎች ሳይነጹ ፋሲካውን በሉ። ሕዝቅያስም። ምንም እንደ መቅደሱ ማንጻት ባይነጻ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን የሚያቀናውን ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው ብሎ ስለ እነርሱ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሕዝቅያስን ሰማው፥ ሕዝቡንም ፈወሰ።
30
Pause     Prev     Next