Bible Verses by Topic

ጮክ ብለው የሚነበቡ/የሚነገሩ ጥቅሶች

መዝሙር 130:1-8
አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ። አቤቱ፥ ድምፄን ስማ፤ ጆሮህ የልመናዬን ቃል የሚያደምጥ ይሁን። አቤቱ፥ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል? ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና። አቤቱ፥ ስለ ስምህ ተስፋ አደረግሁህ፤ ነፍሴ በሕግህ ታገሠች። ከማለዳው ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት ነፍሴ በእግዚአብሔር ታመነች። ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት፥ በእርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን ነውና እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመን። እርሱም እስራኤልን ከኃጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።
30
Pause     Prev     Next